ስለ ማርቆስ ወንጌል

የማርቆስ ወንጌል የናዝሬት ኢየሱስ በጣም ጥንታዊው የጽሑፍ መዝገብ ነው፣ በኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የቅርብ ጓደኛ ፔትሮስ በ65 ዓ። ማርቆስ የቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ አካል ነው - የአዲሱ ኪዳን ሁለተኛው መጽሐፍ። 16 በድርጊት የተሞሉ ምዕራፎቹ የኢየሱስን ልዩ ማንነት፣ ማስተማር እና ስራዎች ያሳያሉ። ወንጌል ማለት 'መልካም ዜና' ማለት ነው፣ እናም ማርቆስ ይህንን መጽሐፍ «ስለ ኢየሱስ መሲያስ መልካም ዜና» እንደሆነ ይገልጻል።

ወንጌል ምንድን ነው?

ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ሰዎች ለኃጢአታችን ጥፋት እና ፍርድ እንደሚገባቸው ያስተምረናል። መልካም ዜናው ግን ኢየሱስ መስቀል ላይ ሞቶ የሚገባንን ፍርድ ወሰደ ነው። ለሚያመን ሁሉ ኃጢአት እንደከፈለ ለማረጋገጥ በሶስተኛ ቀን ከሞቱ ተነሳ። እና ኢየሱስን እንደ ጌታ እና አዳኝ ስንታመን እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እና ለዘላለም ይቅረናል። ከእግዚአብሔር ጋር በጭራሽ የማያልቅ እውነተኛ እና የተመለሰ ግንኙነት እናገኛለን።

ለማንበብ ጠቃሚ ምክሮች

ይህንን መጽሐፍ በምዕራፍ እና በጥቅስ ቁጥሮች ማሰስ ይችላሉ (ምዕራፍ ለመቀየር በገጹ ታችኛው ክፍል ያሉትን አገናኞች ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ 'ማርቆስ 8:29' ማርቆስ ምዕራፍ 8፣ ጥቅስ 29 ን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ ከሌላ ቦታ የተሰራ ድሮ መጽሐፍ ስለሆነ በመጀመሪያ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጸልዩ፣ እና ልምድ ያለው የኢየሱስ ተከታይ ጋር መጽሐፉን ማንበብ ያስቡ። እንደ bibleref.com ያሉ የመስመር ላይ አስተያየቶችም በሚማኑበት ጊዜ ሊረዱዎት ይችላሉ።

ማርቆስ

ማርቆስ 12

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
1ከዚያም እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ ዙሪያውን ዐጠረ፤ ለመጭመቂያው ጕድጓድ ቈፈረ፤ የመጠበቂያም ማማ ሠራለት፤ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 2በመከር ጊዜም ከወይኑ ፍሬ እንዲያመጣለት ባሪያውን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። 3እነርሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት። 4እንደ ገናም ሌላ ባሪያ ላከ። እነርሱም ራሱን ፈንክተውና አዋርደው መለሱት። 5አሁንም እንደ ገና ሌላ ላከ፤ ይህኛውንም ገደሉት፤ ከሌሎች ከብዙዎቹ መካከል አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹንም ገደሉ።
6 “አሁንም የሚላክ ሌላ ነበረው፤ እርሱም የሚወድደው ልጁ ነበረ፤ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት ከሁሉ በኋላ ላከው።
7 “ገበሬዎቹ ግን እርስ በርሳቸው፣ ‘ይህማ ዋናው ወራሹ ነው፤ ኑ እንግደለው፤ ርስቱ የእኛ ይሆናል’ ተባባሉ፤ 8ከዚያም ይዘው ገደሉት፤ ከወይኑ ስፍራም አውጥተው ጣሉት።
9 “እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል። 10እንዲህ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል አላነበባችሁምን?
“ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣
እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ፤
11 ጌታ ይህን አድርጓል፣
ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’ ”
12ምሳሌውን የተናገረው ስለ እነርሱ መሆኑን ስላወቁ፣ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ስለ ፈሩ ትተዉት ሄዱ።
13ከዚያም በነገር እንዲያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ። 14እነርሱም መጥተው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛ ሰው መሆንህን፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉንም እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤ ይልቁንስ የእግዚአብሔርን መንገድ ብቻ በእውነት ታስተምራለህ፤ ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም? 15እኛስ እንክፈል ወይስ አንክፈል?”
ኢየሱስ ግን ግብዝነታቸውን ዐውቆ፣ “ለምን ልታጠምዱኝ ትፈልጋላችሁ? እስኪ አንድ ዲናር አምጡልኝና ልየው” አላቸው። 16እነርሱም አመጡለት፣ “ይህ የማን መልክ ነው? ጽሕፈቱስ የማን ነው?”
አላቸው፤ እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” አሉት።
17ኢየሱስም፣ “የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው። እነርሱም በርሱ እጅግ ተደነቁ።
18ከዚህ በኋላ ትንሣኤ የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ 19“መምህር ሆይ፤ የአንድ ሰው ወንድም ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ ወንድሙ የሟችን ሚስት አግብቶ ለወንድሙ ዘር እንዲተካ ሙሴ ጽፎልናል። 20ታዲያ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ የመጀመሪያው አግብቷት ዘር ሳይተካ ሞተ፤ 21ሁለተኛውም ሴትዮዋን አገባት፤ እርሱም ዘር ሳይተካ ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤ 22ሰባቱም አገቧት፤ ዘር ግን አልተኩም፤ በመጨረሻም ሴትዮዋ ሞተች። 23እንግዲህ፣ ሰባቱም አግብተዋታልና በትንሣኤ ለማንኛቸው ሚስት ልትሆን ነው?” አሉት።
24ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ የምትስቱ አይደለምን? 25ሙታን በሚነሡበት ጊዜ እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም። 26ስለ ሙታን መነሣት ግን፣ በሙሴ መጽሐፍ ይኸውም ስለ ቍጥቋጦው በተነገረው ክፍል፣ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ያለውን አላነበባችሁምን? 27እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ እጅግ ተሳስታችኋል!”
28ከጸሐፍትም አንዱ መጥቶ ሲከራከሩ ሰማቸው፤ ኢየሱስ ለቀረበለት ጥያቄ ተገቢውን መልስ መስጠቱን አስተውሎ፣ “ለመሆኑ ከትእዛዞች ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ነው?” ሲል ጠየቀው።
29ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከሁሉ የሚበልጠው ይህ ነው፤ ‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ ጌታ አምላካችን፣ ጌታ አንድ ነው። 30አንተም ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህና በፍጹም ኀይልህ ውደድ።’ 31ሁለተኛውም ይህ ነው፤ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።’ ከእነዚህም የሚበልጥ ትእዛዝ የለም።”
32ጸሓፊውም እንዲህ አለው፤ “መምህር ሆይ፤ መልካም ብለሃል፤ እግዚአብሔር አንድ መሆኑን፣ ከርሱም ሌላ አለመኖሩን እውነት ተናግረሃል፤ 33እርሱን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ መውደድ፣ እንዲሁም ባልንጀራህን እንደ ራስህ መውደድ ከሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉና ከሌሎችም መሥዋዕቶች ይበልጣል።”
34ኢየሱስም በማስተዋል እንደ መለሰለት አይቶ፣ “አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም” አለው። ከዚህ በኋላ ሊጠይቀው የደፈረ ማንም አልነበረም።
35ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ አደባባይ በሚያስተምርበት ጊዜ እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበ፤ “ጸሐፍት እንዴት ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው ይላሉ? 36ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ሲናገር፣
“ ‘ጌታ ጌታዬን፣
“ጠላቶችህን ከእግሮችህ በታች
እስከማደርግልህ ድረስ
በቀኜ ተቀመጥ” አለው። ይላል፤’
37 ታዲያ ዳዊት ራሱ ‘ጌታ’ ካለው፣ እንዴት ተመልሶ ልጁ ይሆናል?” ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰማው ነበር።
38ሲያስተምርም እንዲህ አለ፤ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ “ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞርን፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታን፣ 39በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫን፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራን ይፈልጋሉና፤ 40በረዥም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቍታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”
41ኢየሱስ በመባ መክተቻው ሣጥን ትይዩ ተቀምጦ፣ ብዙ ሰዎች ስጦታቸውን ሲያስገቡ ይመለከት ነበር። ብዙ ሀብታሞች ብዙ ገንዘብ አስገቡ፤ 42አንዲት ምስኪን መበለት ግን ከአንድ ሳንቲም የማይበልጡ ሁለት የናስ ሳንቲሞች አስገባች።
43ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት ሙዳየ መባ ውስጥ ሌሎቹ ከጨመሩት የበለጠ አስገባች። 44እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።”

ቀጥሎ ወዴት መሄድ ይፈልጋሉ?