ስለ ማርቆስ ወንጌል

የማርቆስ ወንጌል የናዝሬት ኢየሱስ በጣም ጥንታዊው የጽሑፍ መዝገብ ነው፣ በኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የቅርብ ጓደኛ ፔትሮስ በ65 ዓ። ማርቆስ የቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ አካል ነው - የአዲሱ ኪዳን ሁለተኛው መጽሐፍ። 16 በድርጊት የተሞሉ ምዕራፎቹ የኢየሱስን ልዩ ማንነት፣ ማስተማር እና ስራዎች ያሳያሉ። ወንጌል ማለት 'መልካም ዜና' ማለት ነው፣ እናም ማርቆስ ይህንን መጽሐፍ «ስለ ኢየሱስ መሲያስ መልካም ዜና» እንደሆነ ይገልጻል።

ወንጌል ምንድን ነው?

ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ሰዎች ለኃጢአታችን ጥፋት እና ፍርድ እንደሚገባቸው ያስተምረናል። መልካም ዜናው ግን ኢየሱስ መስቀል ላይ ሞቶ የሚገባንን ፍርድ ወሰደ ነው። ለሚያመን ሁሉ ኃጢአት እንደከፈለ ለማረጋገጥ በሶስተኛ ቀን ከሞቱ ተነሳ። እና ኢየሱስን እንደ ጌታ እና አዳኝ ስንታመን እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እና ለዘላለም ይቅረናል። ከእግዚአብሔር ጋር በጭራሽ የማያልቅ እውነተኛ እና የተመለሰ ግንኙነት እናገኛለን።

ለማንበብ ጠቃሚ ምክሮች

ይህንን መጽሐፍ በምዕራፍ እና በጥቅስ ቁጥሮች ማሰስ ይችላሉ (ምዕራፍ ለመቀየር በገጹ ታችኛው ክፍል ያሉትን አገናኞች ይመልከቱ)። ለምሳሌ፣ 'ማርቆስ 8:29' ማርቆስ ምዕራፍ 8፣ ጥቅስ 29 ን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ ከሌላ ቦታ የተሰራ ድሮ መጽሐፍ ስለሆነ በመጀመሪያ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጸልዩ፣ እና ልምድ ያለው የኢየሱስ ተከታይ ጋር መጽሐፉን ማንበብ ያስቡ። እንደ bibleref.com ያሉ የመስመር ላይ አስተያየቶችም በሚማኑበት ጊዜ ሊረዱዎት ይችላሉ።

ማርቆስ

ማርቆስ 8

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
1በዚያ ጊዜ፣ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ። የሚበሉት ምንም ምግብ ስላልነበራቸው ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ 2“ከእኔ ጋራ ሦስት ቀን ስለ ቈዩና የሚበሉትም ስለሌላቸው ለእነዚህ ሰዎች ዐዝንላቸዋለሁ፤ 3እንዲህ እንደ ተራቡ ወደ ቤታቸው ብሰድዳቸው አንዳንዶቹ ከሩቅ የመጡ ስለ ሆኑ በመንገድ ላይ ዝለው ይወድቃሉ።”
4ደቀ መዛሙርቱም መልሰው፣ “በዚህ ምድረ በዳ እነዚህን ለመመገብ የሚያስችል እንጀራ ከወዴት ይገኛል?” አሉት።
5እርሱም፣ “ስንት እንጀራ አላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።
እነርሱም፣ “ሰባት” አሉት።
6እርሱም፣ መሬት ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቡን አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራ ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቈርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ ዐደሉት። 7እንዲሁም ትንንሽ ዓሣዎች ነበሯቸው፤ እርሱም ዓሣዎቹን ባርኮ እንዲያድሏቸው አዘዘ። 8ሕዝቡም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ። 9በዚያም አራት ሺሕ ያህል ሰዎች ነበሩ፤ ካሰናበታቸውም በኋላ፣ 10ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ጀልባ ገብቶ ዳልማኑታ ወደ ተባለ ስፍራ ሄደ።
11ፈሪሳውያንም ወጥተው ከኢየሱስ ጋራ ይከራከሩ ጀመር። ሊፈትኑትም ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳይ ጠየቁት። 12እርሱም በመንፈሱ እጅግ በመቃተት፣ “ይህ ትውልድ ምልክት የሚፈልገው ለምንድን ነው? እውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም!” አለ። 13ከዚያም ትቷቸው በጀልባ ወደ ማዶ ተሻገረ።
14ደቀ መዛሙርቱ እንጀራ መያዝ ስለ ረሱ፣ ከአንድ እንጀራ በቀር በጀልባ ውስጥ ምንም አልነበራቸውም። 15ኢየሱስም፣ “ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ” ብሎ አዘዛቸው።
16እነርሱም እርስ በርሳቸው፣ “እንዲህ የሚለን እኮ እንጀራ ስለሌለን ነው” ተባባሉ።
17ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እንጀራ ስለሌለን ነው በማለት የምትነጋገሩት ስለ ምንድን ነው? አሁንም አታስተውሉምን? ልብ አትሉምን? ወይስ ልባችሁ ደንድኗል? 18ዐይን እያላችሁ አታዩምን? ጆሮ እያላችሁ አትሰሙምን? አታስታውሱምን? 19ዐምስቱን እንጀራ ለዐምስት ሺሕ ሰው በቈረስሁ ጊዜ ስንት መሶብ ሙሉ ትርፍራፊ አነሣችሁ?”
እነርሱም፣ “ዐሥራ ሁለት” አሉት።
20 “ሰባቱንስ እንጀራ ለአራት ሺሕ በቈረስሁ ጊዜ ስንት መሶብ ሙሉ ትርፍራፊ አነሣችሁ?” አላቸው።
እነርሱም፣ “ሰባት” አሉት።
21እርሱም፣ “እስከ አሁን አላስተዋላችሁም ማለት ነውን?” አላቸው።
22ከዚያም ወደ ቤተ ሳይዳ መጡ፤ ጥቂት ሰዎችም አንድ ዐይነ ስውር ወደ ኢየሱስ አምጥተው እንዲዳስሰው ለመኑት። 23እርሱም የዐይነ ስውሩን እጅ ይዞ ከሰፈር ውጭ አወጣው፤ በዐይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎበት፣ እጁንም በላዩ ጭኖ፣ “ምን የሚታይህ ነገር አለ?” ሲል ጠየቀው።
24እርሱም ቀና ብሎ አይቶ፣ “ሰዎች እንደ ዛፍ ሲንቀሳቀሱ አያለሁ” አለ።
25ኢየሱስም እንደ ገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ። 26ከዚያም፣ “ወደ መንደሩ አትግባ! በመንደሩም ለማንም አትናገር” ብሎ ወደ ቤቱ ሰደደው።
27ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ፊልጶስ ቂሳርያ መንደሮች ሄደ፤ በመንገድ ላይ ሳሉም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሰዎች እኔን ማን ነው ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው።
28እነርሱም፣ “መጥምቁ ዮሐንስ የሚሉህ አሉ፤ ሌሎች ኤልያስ ነው ይሉሃል፤ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” ብለው ነገሩት።
29ቀጥሎም፣ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ ነህ” አለው።
30ኢየሱስም ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው።
31ከዚያም የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል፣ በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እንደሚናቅ፣ እንደሚገደል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ እንደሚነሣ ያስተምራቸው ጀመር። 32እርሱም ይህን በግልጽ ነገራቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።
33ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ደቀ መዛሙርቱን እያየ ጴጥሮስን፣ “አንተ ሰይጣን፤ ወደ ኋላዬ ሂድ! የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በሐሳብህ የለምና” በማለት ገሠጸው።
34ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። 35ነፍሱን ለማዳን የሚወድድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋት ሁሉ ግን ያድናታል። 36ሰው ዓለሙ ሁሉ የርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? 37ለመሆኑ፣ ሰው ለነፍሱ ምን መተኪያ አለው? 38በዚህ ዘማዊና ኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፣ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋራ ሲመጣ ያፍርበታል።”

ቀጥሎ ወዴት መሄድ ይፈልጋሉ?